የዮሴፍ በረከት ያግኝህ (1…)

የእግዚአብሄርን ቃል የሚያውቅ ሁሉ የዮሴፍን በረከት በደስታም በጥንቃቄም ያስተውላል፤ በእርግጥ እግዚአብሄር የረዳው፣ በባእዳን ምድር ከፍ ከፍ ያደረገው፣ በባለጠግነትና በማረግ ያገነነውም እንደርሱ ያለ ሰው የለምና። ዮሴፍ እዚህ ከፍታ እስኪደርስ ግን ምን ገጠመው፣ እንዴት ባለስ ሁኔታ ውስጥ አለፈ? ብሎ የሚጠይቅ ከዚህ ትሁት ሰው ህይወት የሚቀበለው ማስተዋል አስተሳሰቡንና እምነቱን ደግሞ ደጋግሞ እንዲቃኝ ያደርገዋል። በእርግጥ እንደ ዮሴፍ ያለ በረከት …
Continue reading የዮሴፍ በረከት ያግኝህ (1…)

መጨረሻው ዘመን (3…)

ያለነው በመጨረሻው ዘመን ላይ ሲሆን በምንኖርበት በዚህ ጊዜ ውስጥ የሚያሳስብ፣ የሚያስጨንቅ ደግሞ የሚያጸልይና ነቅተን እንዳይወርሰን ልንጠባበቀው የሚገባ በዚህ ጊዜም አለምን ተቆጣጥሮ ያለ የሚያስፈራ የአመጽ ብዛት አለ፦ በዚህ ዘመን በአይናችን እየሆኑ ከምናያቸው ጌታ ከሰጣቸው የመጨረሻው ዘመን ምልክቶች መሃል የአመጽ መብዛት አንዱ አስፈሪ ድርጊት ነው። እግዚአብሄር ግን ለሰው ልጆች አስቀድሞ ያስቀመጠውን ትእዛዝ አልረሳም፦ ዘዳ.30:13-16 ’’ሰምተን እናደርጋት ዘንድ …
Continue reading መጨረሻው ዘመን (3…)

የአብረሃም ዘር(2…)

ባለፈው ጽሁፍ እንደተጠቀሰው የአብርሃም ዘር አብረሃም ከተለያዩ ሚስቶች የተወለዱለትን ልጆች በሙሉ የተመለከተ ቢሆንም በተለይ ግን እግዚአብሄር ለአብርሃም የገባውን የቃል ኪዳን ተስፋ የወረሰውን ዘር በይስሃቅ በኩል የተጠራውን ወገን ይመለከታል። የአብርሃም ዘር የተባለው ወገን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በገባው ቃል ኪዳን በኩል ለአዲስ ኪዳን የመዳን መንገድ እንደሆነ በእግዚአብሄር ቃል ውስጥ ተቀምጦአል። በማቴዎስ ወንጌል መጀመሪያ ላይ ለማሳየት የተሞከረው የትውልድ …
Continue reading የአብረሃም ዘር(2…)

ያለና የሚኖር (2…)

የአዲስ ኪዳን መጽሃፍ መጀመርያ፦ በመጀመርያ ቃል ነበረ ብሉይ ኪዳን ሲጀምር በመጀመርያ እግዚአብሄር ሰማይና ምድርን ፈጠረ ሲል በአዲስ ኪዳን በዮሃንስ ወንጌል መጀመሪያ ላይ በመጀመርያው ቃል ነበር ይላል። ስለዚህ በመጀመሪያው ቃል ከነበር፣ በፍጥረት አፈጣጠር ውስጥም ጅማሬውን እግዚአብሄር እንደጀመረው ካመለከተን ከፍጥረታት በፊት የነበረው ቃል የነበረው እግዚአብሄር ብቻ እንደሆነ እንመለከታለን፤ እግዚአብሄር ያለና የሚኖር መሆኑን ባወጀው መሰረት በፍጥረታት ስራው ጊዜ …
Continue reading ያለና የሚኖር (2…)

መጨረሻው ዘመን (2…)

የመጨረሻ ዘመን፡- የነገሮች ፍጻሚያ የሚመጣበት ዘመን፣ የእግዚአብሄር እቅድ የማጠናቀቂያ ዘመን፣ የእግዚአብሄር የዘላለም እቅድ መገለጫ ጅማሬ/ ዋዜማ፣ የአለም መጨረሻ፣ እግዚአብሄር በዚህ አለም የከፈተውን ፕሮግራም ማጠናቀቂያ፣ የጻድቃን አገር መገለጫ ዋዜማ፣ የዘላለም ጠላት ዲያቢሎስና አጋንንት በዘላለም ቅጣት የሚቀጡበት ፍርድ መባቻ ነው። የአለም ፍጻሜ ምልክት የሚገለጠው፦ የፍጥረቶች ማብቂያ ዘመን መድረሱን ለማሳየት፣ የእግዚአብሄር የዘላለም እቅድ መጀመሪያው ጊዜው እንደደረሰ ለምሳየት፣ እግዚአብሄር …
Continue reading መጨረሻው ዘመን (2…)

የመጨረሻው ዘመን (1…)

የመጨረሻው ዘመን የሚመጣበት ጊዜ በተለይ ለጌታ ደቀ መዛሙርት ዋና ጥያቄ ነው፦ ‘’እርሱም በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው፡- ንገረን፥ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው? አሉት።’’ (ማቴ.24:3) ጌታም ለጥያቄያቸው ግልጽ መልስ ሰጥቶአል፤ በቃሉ እንደተመለከተው ከርሱ በስጋ በምድር መመላለስ ወቅት አንስቶ መጨረሻው እስከሚሆን ድረስ የሚገለጡትን ታላላቅ ነገሮች በምልክትነት ተቀምጠዋል፤ …
Continue reading የመጨረሻው ዘመን (1…)

የአብረሃም ዘር(1…)

የአብረሃም ዘር የሚባለው ወገን በትውልድ አንጻር ያየነው እንደሆነ እየተነጋገርን ያለው የአብረሃምን ልጆችና ከርሱ በኋላ የተከተሉት ወገኖችን የትውልድ መስመር ነው፤ የአብረሃም ታሪክ በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ ትልቅ ትኩረት የተደረገበት መሆኑ መሰረቱ ይህ ሰው ከራሱና ከወገኖቹ ሰዋዊ ፈቃድ ወጥቶ ወደ እግዚአብሄር የዘላለም እቅድ ውስጥ ታዛዥ ሆኖ የገባ በመሆኑ፣ ዘመኑን በሙሉ ለተገለጠለት አምላክ ታማኝ ሆኖ በመኖሩና በቀጣይም የእግዚአብሄር ቃል …
Continue reading የአብረሃም ዘር(1…)

የአይን አምሮትና የሥጋ ምኞት(1…)

የሰው ልጅ በሃጢያት ምክኒያት እግዚአብሄር ካኖረው መንፈሳዊ ስፍራ ሲወድቅ፣ ከጌታ ክብር፣ ድምጽና መገኛ አካባቢ ወዲያው ተባርሮአል፤ ሃጢያት እግዚአብሄር ሊያየው የማይታገሰው አምጽ በመሆኑ አዳም በአምላኩ አካባቢ ከነሃጢያቱ ሊመላለስ አልቻለም ነበር፤ ስለዚህ በሃጢያት በወደቀበት በዚያው ወቅት አዳም ላይ ፍርድ ወድቆበታል፤ በዚያው ወቅት ለአዳም ተሰርቶ የነበረ ስፍራና መልካም ስራም ከርሱ ሃጢያት የተነሳ ተሽሮአል። ከፍርድ በሁዋላ ህይወት ለአዳም አስቸጋሪ …
Continue reading የአይን አምሮትና የሥጋ ምኞት(1…)

መንፈሳዊ ድካም(4…)

በመንፈስ ቅዱስ የተበረታታች ነፍስ ስታመሰግን እንዲህ አለች፦ ‘’ሃሌ ሉያ። ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና እግዚአብሔርን አመስግኑ፤እግዚአብሔር ያዳናቸው፥ ከጠላቶች እጅ ያዳናቸው ይናገሩ።ከምሥራቅና ከምዕራብ፥ ከሰሜንና ከባሕር፥ ከየአገሩ ሰበሰባቸው።ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ ተቅበዘበዙ፤ የሚኖሩበትንም ከተማ መንገድ አላገኙም። ተራቡ ተጠሙም፥ ነፍሳቸውም በውስጣቸው አለቀች። በተጨነቁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው፤… የእግዚአብሔርን ቃል ስለ ዐመፁ፥ የልዑልንም ምክር ስለ ናቁ፥ልባቸው በድካም …
Continue reading መንፈሳዊ ድካም(4…)

መንፈሳዊ ድካም(3…)

በመስማት ድካም እንደተያዝን በነፍሳችን ውስጥ ሃብት ሆነው የተቅመጡ ውድ መንፈሳዊ ነገሮችን ነፍሳችን እንደምታጣ አይተናል። መንፈሳዊ ድካም ውስጣችን ገንግኖ እንደሆንበተለይ የመስማት ጉልበትን በመብላት አማኝ ወገን ከእግዚአብሄር ጋር እንዳይቀራረብ ያደርጋልና ነገሩ ቸል መባል የሚችል አይነት አይሆንም፤ የችግሩ ጽናት ብዙ ጉድለታችንን አመልካች ነውና፤ በየትኛውም አቅጣጫ የሚፈጥረው ተጽእኖም ቀላል አይደለም፦ በርሱ የሚያስፈልገንን መንፈሳዊ ነገር መርጠን፣ ለእኛ የሚመጥን ነገር ለይተንና …
Continue reading መንፈሳዊ ድካም(3…)