የአዲስ ኪዳን ህያው አገልግሎት [2/2]

የእውነት እውቀት

ከጌታ ሞት፣ ትንሳኤና እርገት አስቀድሞና ደቀምዛሙርት ለአገልግሎት ሳይወጡ በፊት አስፈሪ ስብራት በይሁዳ ላይ ወድቆአል፡፡ የአዲስ ኪዳን አገልግሎት ላይ እግዚአብሄር ይበልጥ ትኩረትና ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ገና ወንጌል መሰበክ ሳይጀምር ታየ፤ ይሄ ክስተት በደቀመዛሙርቱ ዘንድ ይበልጥ ፍርሀትን፣ ጥንቃቄንና የእግዚአብሄርን ፊት ወደ መፈለግ አምጥቶአል፡፡የሁለቱን ኪዳኖች አገልግሎት በተመለከተ ግን ሀዋርያው ጳውሎስ እያነጻጸረ የሚገልጠው ምስጢር አለው፣ እንዲህ ይላል፡-
2ቆሮ.3:5-17 ”ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፥ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም? የኵነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ፥ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና። ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚህ ነገር ክብሩን አጥቶአልና። ያ ይሻር የነበረው በክብር ከሆነ፥ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ሆኖአልና። እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን እጅግ ገልጠን እንናገራለን፥የዚያንም ይሻር የነበረውን መጨረሻ ትኵር ብለው የእስራኤል ልጆች እንዳይመለከቱ፥ በፊቱ መጋረጃ እንዳደረገ እንደ ሙሴ አይደለንም። ነገር ግን አሳባቸው ደነዘዘ። ብሉይ ኪዳን ሲነበብ ያ መጋረጃ ሳይወሰድ እስከ ዛሬ ድረስ ይኖራልና፤ በክርስቶስ ብቻ የተሻረ ነውና።”
ጳውሎስ ብዙ ጸጋ የበዛለት አገልጋይ ነበረ፡፡ ሌሎች እንዲድኑ ሙሉ ጥረቱንና ጊዜውን እስከማውጣት ፈቅዶአልም፡፡ ያም ሆኖ ግን ለሌሎች መዳን ምክኒያት ከሆነ በሁዋላ እርሱ ደግሞ የተጣለ እንዳይሆን እንደሚተጋ ተናግሮአል፡፡ ለምን እንዲህ ይናገራል? የሚያገለግለው ህያው አምላክን ስለሆነ፣ እግዚአብሄር እርሱ ፍቅር ቢሆንም የሚበላ እሳትም ስለሆነ፡፡
ዕብ.10:26-31 ”የእውነትን እውቀት ከተቀበልን በኋላ ወደን ኃጢአት ብናደርግ ከእንግዲህ ወዲህ ስለ ኃጢአት መሥዋዕት አይቀርልንምና፥
የሚያስፈራ ግን የፍርድ መጠበቅ ተቃዋሚዎችንም ሊበላ ያለው የእሳት ብርታት አለ። የሙሴን ሕግ የናቀ ሰው ሁለት ወይም ሦስት ቢመሰክሩበት ያለ ርኅራኄ ይሞታል፤ የእግዚአብሔርን ልጅ የረገጠ ያንንም የተቀደሰበትን የኪዳኑን ደም እንደ ርኵስ ነገር የቆጠረ የጸጋውንም መንፈስ ያክፋፋ፥ እንዴት ይልቅ የሚብስ ቅጣት የሚገባው ይመስላችኋል? በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ ያለውን እናውቃለንና፤ ደግሞም፡- ጌታ በሕዝቡ ይፈርዳል። በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።”
ከምትነድ እሳት ጋር መኖር የሚችል ማን ነው? ሲል ይጠይቃል ቃሉ፤ ማንም ከሌለ ከርሱ ጋር በምህረት እንዴት መኖር እንደሚቻል መማር ያስፈልጋል፡፡ ለማወቅ ይረዳ ዘንድም የሚያኖረውን አምላክ በትህትና መቅረብ፣ ምህረቱን እንዲሰጥና በሞገስ እንዲቀበል መጠማት ተገቢ ነው፡፡ከምንም በላይ ግን የእውነት እውቀት የሆነውን በወንጌል የተሰበከውን የኢየሱስ ክርስቶስ መድሀኒትነትን አምነንና ድነን ህይወቱን ከተቀበልን በኋላ ወደን እርሱን የሚያስክድ ኃጢአት ብናደርግ ሁለተኛ ስለ ኃጢአታችን የሚቀርብ ሌላ መሥዋዕት አይቀርልንም/ሌላ የእግዚአብሄር በግ የለም፣አልተዘጋጀምም፡፡ አዳኙን ጌታ በሚክዱና በማያምኑ ላይ የሚመጣ የሚያስፈራ ፍርድ እርሱም ተቃዋሚዎችን ሊበላ ያለ የእሳት ብርታት እንደተዘጋጀ ያለጥርጥር ማመን ተገቢ ነው፡፡
እግዚአብሄር ያዳናቸው ትሁት አማኞች በአንድነት በአንድ አካል ተመስለዋል፡፡ነገር ግን በአንድ አካል ላይ ብዙ ብልቶች ይገኛሉ፡፡ ብልቶቹ በመንፈስ ሆነው በውህደትና በአንድነት ሲገለጡ አካሉ በሙላት ይገለጣል፡፡ስለ አካሉ ያለን እውቀት ብልቶቹን በሙሉ ማስተዋል ስንችል እንጂ በተወሰኑ ብልቶች እውቀት ስለአካሉ አብዝተን ብንናገር ስህተታችንን እናበዛለን፡፡የአካሉ ምስል እንዲገለጥ/በጽድቅ ቤተክርስቲያን ለአለም እንድትገለጥ የእያንዳንዱ ብልት በክርስቶስ ተሰርቶ በጽድቅ ማደግን ይጠይቃል፡፡ለዚህ እያንዳንዱ ብልት ከሌላው ጋር በእውነት ተጣብቆ በፊቱ እንዲታይ እግዚአብሄር እንደሚቀና በመጀመሪያዪቱ ቤተክርስቲያን ውስጥ በሰራው ስራ አሳይቶአል፣ ይህም ለትምህርታችን ተጽፎ እናገኘዋለን፡-
ሐዋ.5:1-15 ”ሐናንያም የተባለ አንድ ሰው ሰጲራ ከተባለች ከሚስቱ ጋር መሬት ሸጠ፥ሚስቱም ደግሞ ስታውቅ ከሽያጩ አስቀረና እኩሌታውን አምጥቶ በሐዋርያት እግር አጠገብ አኖረው።ጴጥሮስም፡- ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ? ሳትሸጠው የአንተ አልነበረምን? ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለ ምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም አለው።ሐናንያም ይህን ቃል ሰምቶ ወደቀ ሞተም፤ በሰሙትም ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።…ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላም ሚስቱ የሆነውን ሳታውቅ ገባች።ጴጥሮስም መልሶ፡- እስቲ ንገሪኝ፥ መሬታችሁን ይህን ለሚያህል ሸጣችሁትን? አላት። እርስዋም፡- አዎን፥ ይህን ለሚያህል ነው አለች።ጴጥሮስም፡- የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለ ምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው አንቺንም ያወጡሻል አላት።ያን ጊዜም በእግሩ አጠገብ ወደቀች ሞተችም፤ ጐበዞችም ሲገቡ ሞታ አገኙአት አውጥተውም በባልዋ አጠገብ ቀበሩአት።በቤተ ክርስቲያን ሁሉና ይህንም በሰሙ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ።”
ስብራቱ በረከት ወይም ደስታ አልነበረም፣ በቤተ ክርስቲያን ሁሉና ይህንም በሰሙ ሁሉ ላይ ታላቅ ፍርሃት ሆነ እንጂ።የእግዚአብሄርን ባህሪ ያለማወቅ በዚህም ዘመን ለብዙ ጥፋት እያዘጋጀ ይገኛል፡፡የትእቢት ነገር፣ የፈጠራ ነገር፣ እርሱን ያለመፍራትና በሀሰት የመመስከር ነገር፣ ልዩ ወንጌል የመፍጠር ነገር፣ በልዩ መንፈስ የመገልገል ነገር.. ለፍርድ የሚያዘጋጅ ብርቱ ጥፋት ሆኖአል፡፡ ትሁታን ግን እርሱን ለማወቅ በየእለቱ ወደርሱ መቅረብ ይገባቸዋል፡፡መቅረቢያ መንገዱ ህያው ቃሉ ነው፡፡
በአንድ አጋጣሚ ጌታ ኢየሱስ ስለራሱ ሲናገር እኔ በልቤ ትሁትና የዋህ ነኝ አለ፡፡ይህ አነጋገሩ እጅግ የሚያስደስትና የሚያስመካ ነው፡፡ሆኖም ሁልጊዜ ይህንን ማንነቱን በመያዝ ለራሳችን ድካም መጽናኛና መደበቂያ ምክኒያት ማድረግ ይገባናል ወይ? ወይስ የፍርድ ወንበሩ ፊት ሁላችን አንድ ቀን እንድንቆም ጨምረን እናስብ? ሁሉን እንደ ስራው እንዲከፍል በቃሉ ተናገሮ አይደለምን? እርግጥ ነው እርሱ እጅግ መሃሪ ነው፤ ምህረትና ትህትናው ግን ተሰናክለን እንዳንቀር ሊያቀርበንና ሊያኖረን ነው፣ ቅጣቱና ተግሳጹም መንገዱን ይዘን ወደፊት እንድንጉዋዝ ወዳየልንም እንድንገባ ማስተካከያ ነው፡፡ ከዚህ ሌላ የማይቀር መቅሰፍቱ መገለጡ የግድ ነው፤ ከምህረቱ ፈጽመው ለራቁ መዳኑንም ቸል ላሉ ያዘጋጀው ነውና፡፡ያም የዘላለም ቅጣት የማይቀለበስም ፍርድ ነው፡፡
ዕብ.2:1-4 ”ስለዚህ ከሰማነው ነገር ምናልባት እንዳንወሰድ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ያስፈልገናል።በመላእክት የተነገረው ቃል ጽኑ ከሆነ፥ መተላለፍና አለመታዘዝም ሁሉ የጽድቅን ብድራት ከተቀበለ፥ እኛስ እንዲህ ያለውን ታላቅ መዳን ቸል ብንለው፥ እንዴት እናመልጣለን? ይህ በጌታ በመጀመሪያ የተነገረ ነበርና፥ የሰሙትም ለእኛ አጸኑት፥እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ እንደ ፈቀደ በምልክትና በድንቅ ነገር በልዩ ልዩ ተአምራትም፥ መንፈስ ቅዱስንም በማደል አብሮ መሰከረለት።”
ከብሉይ ወደ አዲስ ኪዳን አገልግሎት
ዕብ.8:5-9 ”እነርሱም ሙሴ ድንኳኒቱን ሊሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ። በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ተጠንቀቅ ብሎት ነበርና። አሁን ግን በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሠረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ መካከለኛ እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቶአል። ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር። እነርሱን እየነቀፈ ይላቸዋልና። እነሆ፥ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ኪዳን የምገባበት ወራት ይመጣል ይላል ጌታ፤ከግብፅ አገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው ይላል ጌታ።”
የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች
2ቆሮ.3:5-12 ”ብቃታችን ከእግዚአብሔር ነው እንጂ፥ በገዛ እጃችን እንደሚሆን አንዳችን እንኳ ልናስብ ራሳችን የበቃን አይደለንም፤እርሱም ደግሞ በመንፈስ እንጂ በፊደል ለማይሆን ለአዲስ ኪዳን አገልጋዮች እንሆን ዘንድ አበቃን፤ ፊደል ይገድላልና መንፈስ ግን ሕይወትን ይሰጣል።ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ፥የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም? የኵነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ፥ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና።ያ የከበረ እንኳ እጅግ በሚበልጠው ክብር ምክንያት በዚህ ነገር ክብሩን አጥቶአልና።ያ ይሻር የነበረው በክብር ከሆነ፥ ጸንቶ የሚኖረውማ እጅግ ይልቅ በክብር ሆኖአልና።እንግዲህ እንዲህ ያለ ተስፋ ካለን እጅግ ገልጠን እንናገራለን፡፡”
ስብራትን የሚያሻግር የእግዚአብሄር የምህረት አሰራር በጸጋ ተገለጠ
ሮሜ.12:6-8 ”እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤ የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር።”
ያለመታከት በእውነት የሚያሮጥ አገልጋይን የእግዚአብሄር ጸጋ ያግዘዋል
2ቆሮ. 4:1-3 ”ስለዚህ ምክንያት ምሕረት እንደ ተሰጠን መጠን ይህ አገልግሎት ስላለን አንታክትም። ነገር ግን የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናልና በተንኮል አንመላለስም የእግዚአብሔርንም ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናመሰግናለን። ወንጌላችን የተከደነ ቢሆን እንኳ የተከደነባቸው ለሚጠፉ ነው።”
የአዲስ ኪዳን አገልግሎት መከራ ከመቀበል ጋር በጸጋ አገልግሎት ነው
2ጢሞ. 4:3-8 ”ሕይወት የሚገኝበትን ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ፥ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን ያከማቻሉ። እውነትንም ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ፥ ወደ ተረትም ፈቀቅ ይላሉ። አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም። በመሥዋዕት እንደሚደረግ፥ የእኔ ሕይወት ይሠዋልና፥ የምሄድበትም ጊዜ ደርሶአል። መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ፥ ሩጫውን ጨርሼአለሁ፥ ሃይማኖትን ጠብቄአለሁ፤ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፥ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፥ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።”
እግዚአብሄር ከአዲስ ኪዳን አገልግሎት የሚጠብቀው
ራእ.2:19-22 ”ሥራህንና ፍቅርህን እምነትህንም አገልግሎትህንም ትዕግሥትህንም ከፊተኛውም ሥራህ ይልቅ የኋለኛው እንዲበዛ አውቃለሁ። ዳሩ ግን፦ ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ንስሐም እንድትገባ ጊዜ ሰጠኋት ከዝሙትዋም ንስሐ እንድትገባ አልወደደችም። እነሆ፥ በአልጋ ላይ እጥላታለሁ፥ ከእርስዋም ጋር የሚያመነዝሩትን ከሥራዋ ንስሐ ባይገቡ በታላቅ መከራ እጥላቸዋለሁ”
በአዲስ ኪዳን የተገለጠ መቅሰፍት ሲታወስ
ሐዋ.1:15-19 ”በዚህም ወራት ጴጥሮስ መቶ ሀያ በሚያህል በሰዎች ማኅበር አብረው በነበሩ በወንድሞቹ መካከል ተነሥቶ አለ። ወንድሞች ሆይ፥ ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤ ከእኛ ጋር ተቈጥሮ ነበርና፥ ለዚህም አገልግሎት ታድሎ ነበርና። ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም የደም መሬት ማለት ነው።”
የእግዚአብሄር ህዝብ አገልግሎት
ሮሜ.12:1-2 ”እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።”
ጥንቃቄ ያስፈልጋል
ዕብ.12:25-29 ”ለሚናገረው እምቢ እንዳትሉ ተጠንቀቁ፤ እነዚያ በምድር ላስረዳቸው እምቢ ባሉ ጊዜ ካላመለጡ፥ ከሰማይ ከመጣው ፈቀቅ የምንል እኛስ እንዴት እናመልጣለን? በዚያም ጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጠ፥ አሁን ግን፡- አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል። ዳሩ ግን፡- አንድ ጊዜ ደግሜ የሚል ቃል፥ የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት የተፈጠሩ እንደሚሆኑ ይለወጡ ዘንድ ያሳያል። ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።”
በማጠቃለያው የከበረውን ከተዋረደው ያለመለየት ከባድ መዘዝ ማስከተሉን አይተናል፡፡ አንዳንዶች በመዘናጋት እንደሚሉት ”ምን ችግር አለው፣ እግዚአብሄር አንተ እንደምትለው ጨካኝ አይምሰልህ… ”ማለት ጥፋትን ያለባህሪው ማሽሞንሞን ነውና እንዲህ ካለው አመለካከት በፍጥነት መውጣት ያስፈልጋል፡፡