በመጨረሻው ቀን በቤተክርስቲያን ውስጥ አስቸጋሪ ባህሪያት እንደሚመጡ እንዲህ በግልጥ ተነግሮአል፡፡እነዚህ ባህሪዎች በእኛ ትውልድ ውስጥ እየታዩ ካሉት ጋርሲነፃፀሩ ምን ይመስላሉ? በእኛ በራሳችን ላይ አየነገሰ ያለ ነገር ምንድነው? እውነተኛ ሆነን ራሳችንን ስናይ ከእኛ መወገድ የሚገባው አላስፈላጊ ነገር እንዳለ ይታየናል? ምልክቶቹ በስፍራና በፆታ ስለማይለያዩ እንደ ትውልድ በአንድነት እንደ ግለሰብም እያንዳንዳችን ነገሩን አስተውለን እንድንጉዋዝ እንዲሁም በእነዚህ አስጨናቂ ባህሪዎች አንዳችንም እንዳንወረስ ምክኒያትን እያስወገድን በጥንቃቄ የምንመላለስበትን የእግዚአብሄር ፀጋ መያዝ ይገባናል፡፡በዚህ መንፈስም ቀጥሎ የምናገኛቸውን የመጨረሻው ቀን ምልክቶች እንመልከት፡-
1ኛውየመጨረሻ ቀን ምልክት:- ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉ
በእኛ ትውልድ የዚህ ችግር ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሶአል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ብዙ ሰዎች የራስ ጥቅምን ካማከለ ግንኙነት ውጪ ፈቀቅ የማይሉበት ደረጃ ላይ ይገኛሉ፡፡ይህ ደግሞ ራስን ከመውደድ የሚመነጭ ስህተት ነው፡፡ስለ ሰው ቸልተኛ መሆን፣ በራስ ጉዳይ ላይ ብቻ ንቁ መሆንና የራስን ነገር በምንም መልኩ አሳልፎ ያለ መስጠት ዝንባሌ፣ በብልጠትም በጉልበትም ለራስ ጉዳይ ብቻ መትጋት የተለመደ ሆኖአል፡፡የራስን ብቻ ለመሙላት በሚደረግ ጥድፊያ የሌላን የመጥፋት አጋጣሚ ይፈጥራል፡፡ራስን ማስቀመጥ ከሌላው መሀል አድርጎ እንጂ ተነጣጥሎ የራስን ጉዳይ ለማስፈፀም መሮጥ ሌላ ሰውን እየጎዱና እያሳዘኑ እንዲራመዱ የሚያደርግ ነው፡፡የሰውን ቀልብ እየገዙ ያሉት ሚድያዎች ግለሰባዊነትን አብዝተው የሚያራግቡ ናቸው፡፡ግለሰቦች ስላላቸው ዝና፣ ገንዘብ፣ ስልጣንና የመሳሰለውን በሰፊው ሰለሚዘግቡ እለት እለትምሰውን ስለሚሰበኩ ራስ ወዳድነትን አፋፍተዋል፡፡በነሱ ስብከትብዙ ሰው ሳያስበው በራስ ማፍቀር አባዜ ውስጥ እንዲጠመድ አድርገዋል፡፡ ሌላውን እየጨፈላለቀ የራሴ የሚለውን እንዲነጥቅ የሚገፋፋ ስሜት ፈጥረዋል፡፡
ዛሬ ዛሬ ሰዎች ራሳቸውን በተሳሳተ መንገድ እንዲመለከቱ በእምነት ውስጥ ያሉ ሰባኪዎች ሳይቀሩ ይገፋፋሉ፡፡እነዚህ ሰባኪዎች ህብረትን፣መረዳዳትና ፍቅርን የሚያነሳሱ ሳይሆኑ አማኞች ራሳቸውንና ስለራሳቸው ጉዳይ ብቻ እንዲጨነቁ የሚያበረታቱ ናቸው፡፡አማኞችን ከመከባበር ከመተሳሰብና ከመረዳዳት ይልቅ ራስ ወዳድ እንዲሆኑ የሚያደርጉ ናቸው፡፡በየፀሎት ቤቶች የራስ አጥርን የመገንባት ብልሀት በሰፊው ስለሚሰበክሰዎች ለአምልኮ ሲሰበሰቡ ራስ መውደድን የሚማሩ እንጂ የእግዚብሄርን ፈቃድ አውቀው የሚራመዱ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ከቤተሰብ ወይም ከወዳጅ በተሰጠ ግብዣ ወይም ግፊት ወደተለያዩ ፀሎት ቤቶች የሚጎርፉ ሰዎች እንደዚያ ባለ የስህተት አስተምህሮ ላይ ስለሚወድቁ፣ በዚያምክኒያትም ትክክለኛውን የእግዚአብሄር አላማ ስለማያስተውሉ በመጨረሻ በተሳሳተ አምልኮና አመለካከት ይጠለፋሉ፡፡በተለይራስ ወዳድነትን ከቤተክርስቲያን ማስወገድ ካስፈለገ እርስ በርስ መፈላለግ፣ መከባበር፣ መዋደድ፣ መተሳሰብና መረዳዳት በእውነተኛይቱ ቤተክርስቲያን ውስጥ መንገስ አለበት፡፡
በ1ጢሞ.6፡17-18 ውስጥ እንደተፃፈው ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ሰውን በመርዳትና በማካፈል እግዚአብሄርንሊያከብሩና ደስ ሊያሰኙ እንጂ እሱ የሰጣቸውንለራሳቸው ብቻ ሊጠብቁትእንዳይደለ የእግዚአብሄር ቃል ይመክራል:-እራስን ባልንጀራንም በመውደድ ሁለቱንም አብሮ ማስኬድና የራስወዳድነት እስራትን ማስወገድ ትልቅ ድል ስለሆነ፡፡