1.በጎ ሥጦታ
ስጦታ ከለጋስ አካል የሚወጣ ጥቅም ሆኖ በሰጪው ቸርነት ላይ የተመሰረተ የመስጠት እንቅስቃሴ ነው። ስጦታ ለሰጪውም ለተቀባዩም የሚያስደስት እንድምታ አለው። ማንም የሚሰጥ አካል አምኖበት የሚሰጥ ሲሆን ተቀባዩ ክብደት ሰጥቶ ሰጪውን የሚያከብርበት አጋጣሚ ነው። አንድ ሰጪ ለሌላው ተቀባይ እንደዚህ ባለ መንገድ ስጦታ ሊሰጠው ይችላል።
እግዚአብሄር ሊባርክ ይሰጣል
ዘፍ.17:15-16 ”እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፡- የሚስትህን የሦራን ስም ሦራ ብለህ አትጥራ፥ ስምዋ ሣራ ይሆናል እንጂ።እባርካታለሁ፥ ደግሞም ከእርስዋ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ እባርካትማለሁ፥ የአሕዛብም እናት ትሆናለች፤ የአሕዛብ ነገሥታት ከእርስዋ ይወጣሉ።”
ሰው ለእግዚአብሄር የምስጋና መስዋእት ይሰጣል
ዘፍ.28:20-22 ”ያዕቆብም እንዲህ ብሎ ስእለት ተሳለ፡- እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ቢሆን፥ በምሄድባትም በዚች መንገድ ቢጠብቀኝ፥ የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ፥ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፤ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።”
ለእግዚአብሄር አገልግሎት ስጦታ በውዴታ ይሆናል
1ዜና.21:23፤ ”ኦርናም ዳዊትን፡- ለአንተ ውሰደው፥ ጌታዬ ንጉሡም ደስ የሚያሰኘውን ያድርግ፤ እነሆ፥ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሬዎቹን፥ ለእንጨትም የአውድማውን ዕቃ፥ ከእህልም ቍርባን ስንዴውን እሰጥሃለሁ፤ ሁሉን እሰጣለሁ አለው።”
በጎ ስጦታ ሁሉ ከእግዚአብሄር ነው
2ዜና.1:11-12 ”እግዚአብሔርም ሰሎሞንን፡- ይህ በልብህ ነበረና፥ ባለጠግነትንና ሀብትን ክብርንና የጠላቶችህን ነፍስ ረጅምም ዕድሜን አልለመንህምና፥ ነገር ግን ባነገሥሁህ በሕዝቤ ላይ ለመፍረድ ትችል ዘንድ ጥበብንና እውቀትን ለራስህ ለምነሃልና ጥበብንና እውቀትን ሰጥቼሃለሁ፤ከአንተ በፊትም ከነበሩት ከአንተም በኋላ ከሚነሡት ነገሥታት አንድ ስንኳ የሚመስልህ እንዳይኖር ባለጠግነትንና ሀብትን ክብርንም እሰጥሃለሁ አለው።”
2.የሃጢያት ስጦታ
ስራ ሰሪው የሰራውን በጎ ነገር ከመቀበል ባለፈ ያልሰራውን ሊያገኝ ቢያልም ወይም የማይገባ ስራ ሰርቶ ዋጋ ቢቀበል የሃጢያት ስጦታን አግኝቶአል ያስብላል። የሃጢያት ስጦታ ተገቢነት የሌለው ስጦታና በአመጽ የሚገለጥ አቅርቦት ነው።ሃጢያት ስጣታ ላይ ሲገለጥ ስጦታም በሃጢያት ምክኒያት ሲገኝ ስጦታን አሸማቃቂ ያደርገዋል።ሃጢያት መተላለፍ ሆኖ በእግዚአብሄር ዘንድ ቁጣን እንደማምጣቱ በመተላለፍ የተገኘው ስጦታም የግለሰቡን ኪስ ይሙላ እንጂ ከዚያ አልፎ ለነፍስ የሚተርፍ ክፉ ነገር መሸመቻ ነው። መገዛት ሲሳነን፣ ፍቅር ሳይገዛን፣ ለወንድማማችነት ሳንራራ፣ መጠበቃችን አደብ ሲያጣ፣ በምኞት ራስችንን ማጦዝ ማቆም ሲሳነን ማካካሻ የሚሆን አዲስ ዘዴ እንቀይሳለን፣ ያም የሀጢያት ስጦታ ሸመታ ነው፡፡
የሀጢያተኛ ስጦታ ግን ከእግዚአብሄር ያርቃል
1ነገ.13:7-12 ”ንጉሡም የእግዚአብሔርን ሰው፡- ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ና እንጀራም ብላ፥ በረከትም እሰጥሃለሁ አለው። የእግዚአብሔርም ሰው ንጉሡን፡- የቤትህን እኩሌታ እንኳ ብትሰጠኝ ከአንተ ጋር አልገባም፥ በዚህም ስፍራ እንጀራ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም፤እንጀራ አትብላ፥ ውኃም አትጠጣ፥ በመጣህበትም መንገድ አትመለስ በሚል በእግዚአብሔር ቃል ታዝዤአለሁና አለው።በሌላም መንገድ ሄደ፥ ወደ ቤቴልም በመጣበት መንገድ አልተመለሰም።…”
ጠላት ከእግዚአብሄር ይዞታ ሊያፈናቅል ይንቀሳቀሳል
1ነገ.20:2 ”አክዓብም ናቡቴን፡- በቤቴ አቅራቢያ ነውና የአትክልት ቦታ አደርገው ዘንድ የወይን ቦታህን ስጠኝ፤ ስለ እርሱም ከእርሱ የተሻለ የወይን ቦታ እሰጥሃለሁ፤ ወይም ብትወድድ ግምቱን ገንዘብ እሰጥሃለሁ ብሎ ተናገረው።”
ለጥፋት ተላልፎ መሰጠት
ሕዝ.35:6 ”ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና ለደም አሳልፌ እሰጥሃለሁ ደምም ያሳድድሃል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ደምን ስላልጠላህ ደም ያሳድድሃል።”
የዲያቢሎስ ስጦታ ያሰግዳል
ማቴ.4:8-9 ”ደግሞ ዲያቢሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ፡- ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።”