ብቸኛና ፍጹም ሀይማኖት(4…)

የእግዚአብሄር ፈቃድ

Faith (ሃይማኖት)
– stand fast in the faith- በሃይማኖት ቁሙ
– obedient to the faith- ለሃይማኖት የታዘዙ
– he had opened the door of faith unto the Gentiles- ለአሕዛብ የሃይማኖትን ደጅ ከፈተላቸው
– Examine yourselves, whether ye be in the faith- በሃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ
– the household of faith- የሃይማኖት ቤተ ሰዎች
– One Lord, one faith, one baptism- አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት
– with one mind striving together for the faith of the gospel- በአንድ ልብ ስለ ወንጌል ሃይማኖት አብራችሁ እየተጋደላችሁ
የሃይማኖት (Faith) አግባብነት
የመንፈሳውያን የጋራ እምነት መጠሪያ ሃይማኖት ነው፤ እምነትና ሃይማኖት አንድ ናቸው። በእስራኤል ምድር በተቀጣጠለው የጌታ ኢየሱስ ሃይማኖት (እርሱን በማመን የተፈጠረ እምነት) በአማኞች ዘንድ ከአህዛብም ከወገኖቻቸውም ከፍተኛ ስደት አቀጣጥሎአል፤ ሃዋሪያቶች ግን ለምእመኖች በሃይማኖት ስለመጽናት አጥብቀው ያሳስቧቸው ነበር፦
‘’አይሁድ ግን ከአንጾኪያና ከኢቆንዮን መጡ፤ ሕዝቡንም አባብለው ጳውሎስን ወገሩ የሞተም መስሎአቸው ከከተማ ወደ ውጭ ጐተቱት።ደቀ መዛሙርት ግን ከበውት ሳሉ፥ ተነስቶ ወደ ከተማ ገባ። በነገውም ከበርናባስ ጋር ወደ ደርቤን ወጣ። በዚያችም ከተማ ወንጌልን ሰብከው እጅግ ደቀ መዛሙርትን ካደረጉ በኋላ፥ የደቀ መዛሙርትን ልብ እያጸኑ በሃይማኖትም (faith) ጸንተው እንዲኖሩ እየመከሩና፦ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል እያሉ፥ ወደ ልስጥራን ወደ ኢቆንዮንም ወደ አንጾኪያም ተመለሱ። በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው። በጲስድያም አልፈው ወደ ጵንፍልያ መጡ፥ በጴርጌንም ቃሉን ከተናገሩ በኋላ ወደ አጣልያ ወረዱ፥ ከዚያም ስለ ፈጸሙት ሥራ ለእግዚአብሔር ጸጋ አደራ ወደ ተሰጡበት ወደ አንጾኪያ በመርከብ ሄዱ። በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ (door of faith) እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ። ከደቀ መዛሙርትም ጋር አያሌ ቀን ተቀመጡ።’’ (ሃስ. 14:19-28)
ሃዋርያው ጳውሎስ በሃይማኖት ስር መስደድ እንደሚገባ ያሳስብ ነበር፤ ምክኒያቱም ከጌታ ጋር ለመጓዝ፣ እርሱን ለማገልገል፣ የክብር ህይወት ለመኖርም መሰረታዊ በመሆኑ ይህንን አጥብቆ ተናግሮአል።
‘’ስለ ወንድማችን ስለ አጵሎስ ግን ከወንድሞቹ ጋር ወደ እናንተ ሊሄድ እጅግ አድርጌ ለምኜው ነበር፤ ዛሬም ለመምጣት ከቶ ፈቃድ አልነበረውም፥ ሲመቸው ግን ይመጣል። ንቁ፥ በሃይማኖት ቁሙ (stand fast in the faith) ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ። በእናንተ ዘንድ ሁሉ በፍቅር ይሁን። ወንድሞች ሆይ፥ የእስጢፋኖስ ቤተ ሰዎች የአካይያ በኩራት እንደ ሆኑ ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ’’ (1ቆሮ. 16:12-15)
ሃውርያው ወደ ሚጉዋዝበት ቤተክርስቲያን በመጣ ጊዜ አማኞች ሆነው ሊያያቸው በሚጓጉዋበት ሁኔታ ውስጥ እንዳይሆኑ ይጨነቃል፤ በእግዚአብሄር ቤት ውስጥ እምነትን የሚያናጋ አካሄድ እንዳይፈጠር ሆኖም ከሆነ ስር እንዳይሰድ ወንድሞችን ያሳስባል፤ እንዲህም ይላቸዋል፦
‘’ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም ነገር ግን በእናንተ ኃይለኛ ነው። በድካም ተሰቅሎአልና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በሕይወት ይኖራል። እኛ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንደክማለንና፥ ነገር ግን ስለ እናንተ በሆነ በእግዚአብሔር ኃይል ከእርሱ ጋር በሕይወት እንኖራለን። በሃይማኖት (faith) ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ወይስ ምናልባት የማትበቁ ባትሆኑ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ እንዳለ ስለ እናንተ አታውቁምን? (1ቆሮ. 13:1-5)
ቆላ1፡19-23 ‘’እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና። እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ። ይህም፥ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ ከሰማችሁትም ከወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ፥ በሃይማኖት ጸንታችሁ ብትኖሩ ይሆናል። ያም ወንጌል ከሰማይ በታች ባለው ፍጥረት ሁሉ ዘንድ የተሰበከ ነው፥ እኔም ጳውሎስ የእርሱ አገልጋይ ሆንሁ።’’
Belief/unbelief- ማመን፣ መታዘዝ/አለማመን፣ አለመታዘዝ
– salvation through sanctification of the Spirit and belief of the truth- በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን መዳን
– God hath concluded them all in unbelief- እግዚአብሄር ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታል
-help thou mine unbelief- አለማመኔን እርዳው
-Because of your unbelief- ስለ እምነታችሁ ማነስ ነው
የማመንና የመታዘዝ (Belief/unbelief) አግባብነት
ጌታ ኢየሱስ ማን መሆኑን በሙሉ ልብ ተቀብለን በጊዜው፣ በሁኔታ መሃከል፣ በነገሮች በተጨናነቅንበት ሰአት ግን መፍትሄ እርሱ መሆኑ የማይመጣልን ወቅት አለ። ከዚህ የከፋው ደግሞ በእርሱ መገኘት አካባቢ ያሉ ክንዱን የሚያንቀሳቅሱ ሰዎች በእምነት ማነስ ምክኒያት መጉደል ሲሆንባቸው ነው፣ አለማመናቸው ሌላውን ሊያሰናክል የሚችልበት አጋጣሚም ሲፈጠር እናያለን፦
‘’ከሕዝቡ አንዱ መልሶ፦ መምህር ሆይ፥ ዲዳ መንፈስ ያደረበትን ልጄን ወደ አንተ አምጥቼአለሁ፤ በያዘውም ስፍራ ሁሉ ይጥለዋል፤ አረፋም ይደፍቃል፥ ጥርሱንም ያፋጫል ይደርቃልም፤ እንዲያወጡለትም ለደቀ መዛሙርትህ ነገርኋቸው፥ አልቻሉምም አለው። እርሱም መልሶ፦ የማታምን ትውልድ ሆይ (faithless generation)፥ እስከመቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት አላቸው። ወደ እርሱም አመጡት። እርሱንም ባየ ጊዜ ያ መንፈስ ወዲያው አንፈራገጠው፤ ወደ ምድርም ወድቆ አረፋ እየደፈቀ ተንፈራፈረ።አባቱንም። ይህ ከያዘው ስንት ዘመን ነው? ብሎ ጠየቀው። እርሱም። ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው፤ብዙ ጊዜም ሊያጠፋው ወደ እሳትም ወደ ውኃም ጣለው፤ ቢቻልህ ግን እዘንልን እርዳንም አለው። ኢየሱስም፦ ቢቻልህ ትላለህ፤ ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው። ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ፦ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው አለ (I believe; help thou mine unbelief)።’’ (ማር. 9:17-25)
‘’በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ (to every one that believeth) የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና። ጻድቅ በእምነት ይኖራል (live by faith) ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት (from faith to faith) በእርሱ ይገለጣልና። እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና’’ (ሮሜ.1:19-21)
‘’እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው። አስቀድሞ የእግዚአብሔር ቃላት አደራ ተሰጡአቸው። ታዲያ ምንድር ነው? የማያምኑ ቢኖሩ (not believe?) አለማመናቸው የእግዚአብሔርን ታማኝነት ያስቀራልን?(shall their unbelief make the faith of God)’’ (ሮሜ.3:1-3)
profession/መታመን
– and hast professed a good profession before many witnesses- በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለት
-consider the Apostle and High Priest of our profession, Christ Jesus- የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ
– let us hold fast our profession- ጸንተን ሃይማኖታችንን እንጠብቅ
መታመን (profession)
‘’መልካሙን የእምነት ገድል ተጋደል( good fight of faith)፥ የተጠራህለትንም በብዙም ምስክሮች ፊት በመልካም መታመን የታመንህለትን( and hast professed a good profession before many witnesses) የዘላለምን ሕይወት ያዝ።’’ (1Tim 6:3-12)
ሃዋርያው ጳውሎስ ወጣቱን አገልጋይ ጢሞቴዎስን ሲያበረታታው በያዘው እምነት እንዲጸና፣ በርሱ ዘንድ ያለውን የዘላለም ህይወት አጥብቆ እንዲይዝ፣ ለሌሎችም ይህን ህይወት በማስተማር ጤናማ ያልሆኑ ትምህርቶች አማኞችን እንዳይበክሉ ይጋደል ዘንድ ያዘዋል፤ ተጋድሎውም የሚከተሉትን ያጠቃልላል፦
– ማንም ልዩ ትምህርት የሚያስተምር ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ጤናማ ቃልና እግዚአብሔርን ለመምሰል በሚስማማ ትምህርት የማይጠጋ ትምህርት ቢያመጣ እንዲገስጽ
– በትዕቢት ተነፍቶ ያለ እውቀት ያለውን፣ ምርመራን በቃልም መዋጋትን እንደ በሽተኛ የሚናፍቅን እንዲስተካከል ማስተማርና መገሰጽ
– ቅንዓትና ክርክር ስድብም ክፉ አሳብም እርስ በርስ መናደድም ይወጣሉና አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ፥ እግዚአብሔርን መምሰል ማትረፊያ የሚሆን ከመሰላቸው ሰዎች ይህ ነገር ይገኛልና ከነርሱ እንዲርቅ
– ኑሮዬ ይበቃኛል ለሚለው ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው ይህን አጥብቆ እንዲዝ በመልእክቱ ያስገነዝበዋል።
‘’ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት(Apostle and High Priest of our profession) ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤ ሙሴ ደግሞ በቤቱ ሁሉ የታመነ እንደሆነ፥ እርሱ ለሾመው የታመነ ነበረ። ቤትን የሚያዘጋጀው ከቤቱ ይልቅ የሚበልጥ ክብር እንዳለው መጠን፥ እንዲሁ እርሱ ከሙሴ ይልቅ የሚበልጥ ክብር የተገባው ሆኖ ተቆጥሮአልና። እያንዳንዱ ቤት በአንድ ሰው ተዘጋጅቶአልና፥ ሁሉን ያዘጋጀ ግን እግዚአብሔር ነው። ሙሴስ በኋላ ስለሚነገረው ነገር ምስክር ሊሆን በቤቱ ሁሉ እንደ ሎሌ የታመነ ነበረ፥ ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው፤እኛም የምንደፍርበትን የምንመካበትንም ተስፋ እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንጠብቅ ቤቱ ነን።’’ (እብ3:1-6)
የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ የተባለው እኛን የእግዚአሄር መቅደስ አድርጎ ይሰራን ዘንድ እርሱን የምንመስልበትን አሰራር የገለጠብን ጌታ በመሆኑ፣ ሃይማኖታችን እርሱን በማመን የተመሰረት እንዲሆን በሁሉ ነገር ፊተኛ ስለሆነ፣ ስጋውን በእምነት ያለበሰን፣ መንፈሱን ያጠጣን፣ በደሙ እለት እለት ሊያጥበንና ሊያነጻን በእግዚአብሄር ፊትም ያለነቀፋ እንድንቆም የአዲስ ኪዳን ሊቀካህናት የሆነ እርሱ በመሆኑ ነው፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን።