ቤተክርስቲያን – ማን ናት ? [church of the living God,2..]

ቤተክርስቲያን

ሐ.የጌታን ምርጫ በተመለከተ፡-እነርሱን ብቻ እንድንሰማ ጌታ እንዳዘዘ ማስተዋል ይገባል፡፡ ጌታ ኢየሱስ የሰው ልጅ በሙሉ ለእነርሱ የወንጌል ስብከት ክብር እንዲሰጥ አጥብቆ ወደ እኛ ትእዛዝ ስድዶአል፡፡

ሉቃ10:16 “የሚሰማችሁ እኔን ይሰማል፥ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል፤ እኔንም የጣለ የላከኝን ይጥላል።”ሲል ተናግሮአል፡፡

ይህን ጥቅስ ካስተዋልን ጌታ ኢየሱስ እኔን የሚሰማ እናንተን ይሰማል አላለም፣ለምን? የጌታ ፍቃዱ በመረጣቸው ሀዋርያት አድሮ መስራት ስለሆነ ነው፡፡ስለዚህ ሀዋርያትን የጣለ በእነርሱ አድሮ የሚሰራውን ኢየሱስን ጣለ ማለት ነው፡፡
2ቆሮ.13:2-3 “ሁለተኛ በእናንተ ዘንድ በነበርሁ ጊዜ እንደ ተናገርሁ አሁንም ደግሞ በሩቅ ስሆን፥ ክርስቶስ በእኔ አድሮ እንዲናገር ማስረጃ ከፈለጋችሁ፥ እንደ ገና ብመጣ እንዳልራራላቸው አስቀድመው ኃጢአት ላደረጉት ለሌሎችም ሁሉ አስቀድሜ ብዬአለሁ፥ አስቀድሜም እላለሁ። ክርስቶስም ስለ እናንተ አይደክምም ነገር ግን በእናንተ ኃይለኛ ነው።”

መ.ስለ አገልግሎታችው ምስክር ቢያስፈልግ፡-መልአክ ቢገለጥልን ስሙአቸው የሚለው እነርሱን/ትምህርታቸውን ብቻ እንደሆነ መታወቅ ስለሚገባ ነው፡፡
በብሉይ ኪዳን መልአክ የእግዚአብሄርን ቃል ወደ ህዝቡ በማምጣት ይታወቃል፡፡በአዲስ ኪዳን ግን መልአክ ተገልጦ ወደ ሀዋርያት ይመራል፣ የሀዋርያትን ወንጌል የሚያጸድቅ/ትክክለኛነት የሚያረጋግጥ ስራ ይሰራል፡፡
ሐዋ.10:3-6 “ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል፡- ቆርኔሌዎስ ሆይ የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው።እርሱም ትኵር ብሎ ሲመለከተው ደንግጦ፡- ጌታ ሆይ፥ ምንድር ነው? አለ። መልአኩም አለው፡- ጸሎትህና ምጽዋትህ በእግዚአብሔር ፊት ለመታሰቢያ እንዲሆን አረገ።አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ።እርሱ ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቍርበት ፋቂው በስምዖን ዘንድ እንግድነት ተቀምጦአል፤ ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል።” አለው፡፡
ሠ.በሰማይ ያለን ምስክር በተመለከተ፡-የእነርሱ ስራ በሰማይ የተረጋገጠ በመሆኑና ልትገለጥ ላለች አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ስማቸው የመሰረቶችዋ መጠሪያ መሆኑ እግዚአብሄር ምን ያህል በእነርሱ አገልግሎት እንደተደሰተ የሚያረጋግጥ መሆኑ ነው፡፡
ጌታ ኢየሱስ ለዚህ የከበረ አገልግሎት የመረጣቸውን አስራ-ሁለት ሀዋርያት የመመረጣቸውን ታላቅነት በዘላለማዊ ክብር ሊያትመው ወዶ የአዲሲቱን ኢየሩሳሌም መሰረቶች በስማቸው ሰይሞታል፡፡
ራእ.21:13-14 “በምሥራቅ ሦስት ደጆች፥ በሰሜንም ሦስት ደጆች፥ በደቡብም ሦስት ደጆች፥ በምዕራብም ሦስት ደጆች ነበሩ።ለከተማይቱም ቅጥር አሥራ ሁለት መሠረቶች ነበሩአት፥ በእነርሱም ውስጥ የአሥራ ሁለቱ የበጉ ሐዋርያት ስሞች ተጽፈው ነበር።”
ስለዚህ ማን ነው የእነርሱን ትምህርት ወደ ጎን አድርጎ እነርሱ በሚገቡበት መንግስት ሊገባ የሚችለው?በተቃራኒው በተለያየ መንገድ ስተው ለሚያስቱት ፍርዱ እንዲህ ይላል፡-
ራእ.21:8 “ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”